loading
ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን በሀገራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንዴሌሉ ተናግረው ከእንግዲህ አካላዊ መራራቅን እንጅ እንቅስቃሴን አንገድብም ብለዋል፡፡
ይሁን እንጅ ከውጭ የሚገቡ ዜጎቻችን ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ማድረግ የግድ ይላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለተገኘው ውጤት ሁሉንም ዜጎቻቸውን አመስግነዋል፡፡ኒው ዚላንድ 1 ሺህ 154 ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ተይዘውባት የነበረ ሲሆን 22 ሰዎች ህይዎታቸውን
አጥተዋል፡፡ ቢቢሲ በዘገባው እንዳስነበበው ኒው ዚላንድ አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰወችን ካስመዘገበች ከ17 ቀናት በላይ ማለፉ ተረጋግጧል፡፡በዚህም የተነሳ በፈረንረጆቹ ማርች 25 በአራት ደረጃዎች ተግባራዊ የሚሆን የእንቅስቃሴ እገዳ ጥላ የነበረ ሲሆን መንግስት እና ህዝቡ ተናቦ በመስራቱ ውጤቱ መልካም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሯ ገልጧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለዜጎቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አሁን ላይ ያለንበት ሁኔታ የመጨረሻ ዋስትና ሊሆን እንደማይችልና በሽታው ዳግም ሊያገረሽ እንደሚችል በመገንዘብ ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ ብለዋል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *