loading
ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ::

ናይጀሪያዊቷ እጩ ተወዳዳሪ ራሳቸወን ከምርጫ አገለሉ::

በቦኩ ሀራም የታገቱ ልጃገረዶችን ለማስመለስ በሚያደርጉት ጥረት ስማቸው ጎልቶ የሚታወቀው ኦቢ ኤዚኩሲሊ ከፉክክሩ የወጡት የቡሀሪን መንግስት ለማሸነፍ ለጠንካራ የጥምረት ፓርቲ ድጋፋቸውን ለመስጠት ነው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ኤዚኩሲሊ ፓርቲያቸው አላይድ ኮንግረስ ፓርቲ ኦፍ ናይጀሪያ ኮሊዥን ፎር ቪያብል ኦልተርኔቲቭ  የተባለ ጥምረት እንዲመስርት ነው ቦታቸውን የለቀቁት፡፡

እኔ ራሴን ከተወዳዳሪነት ያገለልኩበት ዋናው ምክንያት ጥምረቱን ለመርዳት እና በመጭው ምርጫ  ገዥውን ፓርቲ ለማሸነፍ ነው ብለዋል  ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፡፡

እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከሌሎች እጩ ተወዳዳሪ ጓደኞቸ ጋር መክረንበታል ያሉት ኤዚኩሲሊ አዲሱ ጥምረት ናይጀሪያዊያን የሚተማመኑበት ፓርቲ እንዲያገኙ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ብርቱ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ሲጠበቁ ራሳቸውን ማግለላቸው ፉክክሩ በቡሀሪ እና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት አቲኩ አቡበከር መካከል እንዲሆን በር ከፍተዋል የሚሉም አሉ፡፡

ኤዚኩሲሊ ከአሁን ቀደም በሀገራቸው ሁለት ጊዜ በሚኒስርትነት ተሹመው ያገለገሉ ሲሆን በአፍሪካ የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነውም ሰርተዋል፡፡

 

 

መንገሻ ዓለሙ

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *