loading
ናይጀሪያ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ሰዎች  ስማቸው በልዩ መዝገብ እንዲሰፍር ልታደርግ ነው፡፡

ናይጀሪያ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ሰዎች  ስማቸው በልዩ መዝገብ እንዲሰፍር ልታደርግ ነው፡፡

አዲሱ አሰራር ከፆታ ጋር የተያያዘ  ጥቃት አድራሾችን በዳታቤዝ መዝግቦ በማስቀመጥ ፆታን መሰረት ያደረገ  ጥቃትን ለመከላከል ታስቦ ነው የተዘጋጀው ተብሏል፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በዚህ የዳታቤዝ ሲስተም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር ከ2015 ጀምሮ ፆታዊ ጥቃት አድርሰው የተከሰሱ እና የተቀጡ ሰዎች ስም ዝርዝር ይሰፍራል፡፡

በናይጀሪያ ከ4 ሴቶች መካከል አንዷ 18 ዓመት ሳይሞላት ጾታዊ ጥቃት እንደሚደርስባት ዩኒሴፍጥናት ያሳያል፡፡

ይሁን እንጂ ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አብዛኞቹ ለፖሊስ ሪፖርት ስለማይደረጉ አጥፊዎቹ ከመጥፎ ድርጊታቸው መቆጠብ አልቻሉም ይላል ጥናቱ፡፡

የናይጀሪያ መንግስት ይህን ስትራቴጂ መዘርጋቱ ወደፊት ሴቶች ላይ ትንኮሳ እና ጥቃት ለማድረስ የሚያስቡ ግለሰቦች ምዝገባውን በመፍራት ይታቀባሉ የሚል እምነት አሳድሯል፡፡

መንገሻ ዓሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *