ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 ናይጄሪያዊቷ እንስት የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመምራት ጫፍ ላይ ደርሰዋል:: የቀድሞዋ የናይጄሪያ የገንዘብ ሚንስትር ንጎዚ ኦኮንጆ ከደቡብ ኮሪያዋ ተፎካከሪያቸው ጋር የመጨረሻውን ዙር ውድድር ተቀላቅለዋል፡፡ የሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑት ኦኮንጆ እና የመጨረሻው ዙር የደረሱት የኬንያ፣ የሳኡዲ አረቢያ እና የእንግሊዝ ተወዳዳሪዎችን በልጠው በመገኘታቸው ነው፡፡
ሀገራቸውን ደቡብ ኮሪያን በገንዘብ ሚኒስትርነት እያለገሉ የሚገኙት ዩ ሚዩንግ ሂ ደግሞ ሌላዋ ከእስያ የተወከሉ ተቋሙን በዳይሬክተር ጄኔራልነት ለመምራት የተቃረቡ ግለሰብ ናቸው፡፡ ተቋሙን በሀላፊነት ሲመሩ የነበሩት ብራዚላዊው ሮቤርቶ አዝቬዶ የስልጣን ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ በመልቀቃቸው ነው አዲስ አመራር መተካት ያስፈለገው፡፡ የዓለም የንግድ ድርጅት ፍትሃዊ ስራ አይሰራም በማለት ከአሜሪካ ከፈተኛ ወቀሳ የሚደርስበት ሲሆን ሀላፊው ከስራ ለመልቀቃቸው ምክንያት የፕዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተፅዕኖ ነው የሚሉም አልጠፉም፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ እስካሁን በአፍሪካዊት ሴት ተመርቶ የማያውቅ ሲሆን ናይጄሪያዊቷ ተወዳዳሪ ይህን ታሪክ ለመስራት ተቃርበዋል ነው የተባለው፡፡