loading
ኔታኒያሁ እስራኤል የሁሉም ዜጎቿ ሀገር አይደለችም አሉ፡፡

ኔታኒያሁ እስራኤል የሁሉም ዜጎቿ ሀገር አይደለችም አሉ፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ እስራኤል የአይሁዶች እንጂ ዜግነት አለን ለሚሉ ሁሉ ሀገር እንዳልሆነች መናገራቸው ብዙዎቹን እያነጋገረ ነው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እርደዘገበው ኔታናያሁ የሰጡት አስተያየት ከጠቅላላው የእስራኤል ህዝብ 20 በመቶ የሚሆኑትን አረብ እስራኤላዊያን ያገለለ መሆኑ በብዙዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም፡፡

ኔታኒያሁ በቱይተር ገፃቸው የሀገራችን ህግ እንደሚደነግገው እስራኤል የአይሀድ ተወላጆች  ብቻ መሆኗን የሚገልፅ ፅሁፍ አስፍረዋል፡፡

ኔታኒያሁ ይህን ያሉት ሮተም ሴላ የተባለች እስራኤላዊት ተዋናይት እስራኤል የሁሉም ዜጎች ሀገር ናት የሚልመልእክት በኢንስታ ግራም ገጿ መልቀቋን ተከትሎ ነው፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *