loading
ኔታናያሁ በቅርቡ ወደ አፍሪካ እንደሚያቀኑ ተናገሩ

አርትስ 19/03/2011

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታናያሁ የቻድን ወዳጅነት አጥብቀው   እንደሚፈልጉት ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በቅርቡ ወደ ምእራብ አፍሪካ ለመጓዘ ያነሳሳቸው  ጉዳይም ከ 46 ዓመታት በኋላ አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር ደፋ ቀና በሚሉላት ቻድ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው፡፡

ካፈው እሁድ ጀምሮ ቴል አቪቭን ለሶስት ቀናት የጎበኙት የቻዱ ፕሬዝዳን ኢድሪስ ዴቢ በእስራኤል ቆይታቸው ከኔታናያሁ ጋር በፀጥታና በሌሎችም ጉዮች ዙሪያ የተሳካ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

ኔታናያሁ እንደሚሉት በምእራብ አፍሪካ ቦኩ ሀራምን  እንዲሁም የኢራንን ተላላኪ ነው የሚሉትን አይ ኤስ አይ ኤስን በመዋጋት ባላት የላቀ ሚና ቻድ ለእስራኤል የወደፊት ሁነኛ አጋር ናት፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *