አሁንም ትኩረት የሚያሻው የኮቪድ-19 ስርጭት
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳለው ምርመራ ከተደረገላቸው 13 ሺህ 280 ሰዎች መካከል 5 ሺህ 185 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ይህም እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 405 ሺህ 745 ከፍ እንዳደረገው ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
በሌላ በኩል 7 ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 396 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ተሰምቷል፡፡ በሀገራችን በሽታው ከገባ ጀምሮ 6 ሺህ 911 ሰዎች ህይዎታቸው ሲያልፍ ያገገሙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 353 ሺህ 787 መድረሱ ታውቋል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ሁኔታውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ የታየው ቸልተኝነት እንደ ሀገር ዋጋ እያስከፈለን ነው ብሏል፡፡