loading
አለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት እንደተደቀነባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2012 አለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት እንደተደቀነባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።የአለም ምግብ ፕሮግራም ሃላፊ ዴቪድ ቤስሌይም በረሃብ ምክንያት የሚከሰተውን ከፍተኛ ቀውስ ለማስወገድ ፈጣን እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣ ሪፓርት በረሃብ ምክንያት ከ135 ሚሊየን እስከ 250 ሚሊየን ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል አመልክቷል።

የአለም ምግብ ፕሮግራም የረሃብ ስጋት የተደቀነባቸው ሀገራት በኢኮኖሚ ቀውስ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭቶች ተፅዕና የደረሰባቸው 10 ሀገራት ናቸው ብሏል።ሀገራቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ የመን ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ አፍጋኒስታን ፣ቬንዜዌላ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳን፣ ሶሪያ ፣ ናይጀሪያ እና ሀይቲ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።ሪፖርቶች እንዳመለከቱት የደቡብ ሱዳን 61 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ባለፈው ዓመት የምግብ ቀውስ አጋጥሟቸው ነበር ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *