አመንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋዊያንን ከሽብርተኞች ጥቃት መጠበቅ ይገባል የሚል ጥሪ አቀረበ::
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 በተለያዩ ሀገራት የሚደርሱ የሽብር ጥቃቶች በእድሜ የገፉ አረጋዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያለው ተቋሙ፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ እንደ ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ እንዲሁም በአብዛኛው የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ችግሩ ከፋ ነው፡፡
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ገና ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት የሚያደርሰውን ቦኩ ሃራምን አጠፋለሁ ብለው ቃል ቢገቡም እስካሁን አልተሳካላቸውም፡፡ በዓለም ዙሪያ በርካታ ሰዎች ሽብርተኞች በሚያደርሱት ጥቃት ሲገደሉና ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ ማየት የተለመደ ቢሆንም አረጋዊያን የሚከፍሉት ዋጋ ከሁሉም አስከፊ ነው ተብሏል፡፡
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች የሆነው አመንስቲ አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ በናይጄሪያ ነፍጥ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሚሊሻዎች በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ግፍ እንደሚፈፅሙ በማስታወስ ድርጊቱ እንዲቆም ለሀገሪቱ መንግስት ጥሪ አቅረቧል፡፡ እነዚህን አረጋዊያን ከጥቃቱ ለመጠበቅ የሽብርተኞች መስፋፊያ የሆኑ ሀገራት
የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ የሁሉም ሀገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሀላፊነት ነዉ ሲል ተቋሙ አሳስቧል፡፡