loading
አሜሪካ ለገበሬዎቿ ካሳ ልትከፍል ነው

ዋሽንግተን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት ኪሳራ ለደረሰባቸው ገበሬዎች 12 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መወሰኗ ተሰምቷል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው በግብርና የሚተዳደሩ አሜሪካውያን ምርታቸውን ወደ ውጭ ሀገር ልከው እንዳይሸጡ አዲሱ የንግድ እሰጣ ገባ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡
በተለይ የአሜሪካን የግብርና ምርቶች ወደ ሀገሯ ታስገባ የነበረቸው ቻይና፤ ትራ ምፕን ለመበቀል የጣለችው ታሪፍ በገበሬዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮባቸዋል፡፡
የታሪፍ ጭማሪውን ተከትሎ የአኩሪ አተር ዋጋ በ15 በመቶ ቀንሷል፤ በዚህም አምራቾቹ ቅሬታ ገብቷቸዋል፡
ታዲያ የአሜሪካ መንግስት የገበሬዎቹን ምርት በመግዛትና ሌሎች የማስተካከያ ርምጃዎችን በመውሰድ ለመካስ ተገዷል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *