loading
አሜሪካ በአፍሪካ የሰፈነውን ሙስና ለመቀነስ ወጣቶችና ሴቶች ወደስልጣን መምጣት አለባቸው አለች

በአፍሪካ የሰፈነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራር ለመቀነስ በኢትዮጵያ እንደተደረገው ወጣቶች እና ሴቶችን ወደስልጣን ማምጣት ተገቢ መሆኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አምባሳደር ቲቦር ናያጅ እንደተናገሩት የአፍሪካ የሙስና ችግር ሊቀንስ የሚችለው በትውልድ ለውጥ ብቻ ነው። ለዚህም በኢትዮጵያ እንደተደረገው ወጣቶችና ሴቶችን ወደስልጣን ማምጣት ተገቢ ነው ።

አምባሳደር ናያጅ ዛሬ ከአፍሪካ ሃገራት ጋዜጠኞች ጋ በነበራቸው የስልክ ውይይት ወቅት እንደተናገሩት አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ በአንክሮ እየተከታተለችው ነው።

አዲሱ አመራርም በጣም ተስፋ ሰጪ ጅምሮችን እያሳየ ነው ብለዋል  ።

በአፍሪካ ወጣት አመራሮች ወደስልጣን ብቅ እያሉ መሆኑን ጠቅሰው ሙስናን ለመዋጋት ውስጣዊ የባህል ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

አፍሪካ ከየትኛውም ሃብቷ በላቀ ያላት ወጣት ሃይል ለውጥ ማምጣት ይችላል። ለዚህ ደግሞ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት ቲቦር ናያጅ።

የአሜሪካ ኩባንያዎች በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ተሳትፎ በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደሩ አሜሪካ የአፍሪካ የቢዝነስ አጋር ለመሆን ፍላጎት ያላት መሆኑንም ጠቅሰዋል። ለዚህም ጠንካራ ስራ በመስራት ላይ ነን ብለዋል።

ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ሃገራት በራቸውን ሲከፍቱ ደጅ የሚያገኟቸው የአሜሪካ ኩባንያዎችን ነው ይላሉ አምባሳደሩ።  እንደኢትዮጵያ እና ኬንያ ባሉ ሃገራት ገበያ ውስጥም የአሜሪካ ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ተሳትፎ መጀመራቸውን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

የአሜሪካ ኩባንያዎች ወደአፍሪካ ሃገራት ዘልቀው መዋዕለንዋያቸውን በስራ ላይ ለማዋል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም ነው ፒተር ናያጅ የጠቆሙት።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *