አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ወጪዎቸን ለመጋራት በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተባለ፡፡
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ወጪዎቸን ለመጋራት በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ተባለ፡፡
ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ የደረሱበት አዲሱ የወጪ መጋራት በእስያ ለሚገኙ የአሜሪካን ወታደሮች የሚውል በጀት እንደሆነ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
ከዋሽንግትን እንደተሰማው መረጃ ከሆነ አዲሱ ስምምነት በዓይነቱ የተለየ እና ለተፈጻሚነቱም ሁለቱም ሀገራት ቁርጠኛ አቋም አላቸው፡፡
ሲ.ኤን.ኤን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ደቡብ ኮሪያ የምታበረክተውን የገንዘብ መጠን ከፍ በማድረግ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ተስማምታለች ብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት በተጠናቀቀው እና በፈረንጆቹ 2014 በተደረሰው ስምምነት መሰረት በሀገሪቱ ለሚገኙ 28 ሺ 5 መቶ የአሜሪካ ወታደሮች ሴኡል በየዓመቱ 848 ሚሊዮን ዶላር ስታዋጣ መቆየቷ ይታወሳል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት አንስቶ የአሜሪካ ወታደሮች በሀገሪቱ መስፈራቸውን አስታውሰው ከሀገሪቱ ከዚህ በላይ ይጠቃል ብለዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ለሶስት ዓመታት የሚቆይ 891 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ለማዋጣት ከውሳኔ ላይ ቢደርሱም ከዋሽንግተን በኩል ድንገተኛ ተቃውሞ በመግጠሙ ውድቅ ተደርጓል፡፡
ደቡብ ኮሪያ ከምታዋጣው ገንዘብ 70 በመቶ ያህሉ በአሜሪካ ወታደሮች ካምፕ በአስተዳደር፣ በቴክኒክ እና በሌሎች አገልግሎት ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ከ8 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኮሪያውያን ሰራተኞች ደሞዝ ይውላል ተብሏል፡፡