loading
አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአመንስቲ አንተርናሽናልን ሪፖርትን መነሻ አድርጎ ባወጣው መግለጫ በክልሉ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የተፈጸሙ በርካታ ወንጀሎች አሳሳቢ ናቸው ብሏል፡፡መግለጫው አክሎም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ግፍና ወንጀል በሚገባ ተጣርቶ የድርጊቱ
ፈጸሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥር አቅርቧል፡፡

የትኛውም የታጠቀ ሃይል የጦርነቱ አካል ባልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃትና የመብት ረገጣ እንዳያደርሱም ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡ ግጭቱ በአስቸኳይ በማቆም የሰዎች ሰቆቃ እንዲያበቃና ለተቸገሩ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳት በተገቢው ጊዜና ቦታ እንዲደርስ ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች መስራት አለባቸው ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡
ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም ዋሽንግተን ገልጻለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *