loading
አራት የፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር አስረከቡ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 አራት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር ማስረከባችው ተገለጸ፡፡ በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል ከሕዝብ እና ከመንግሥት የተሰጠን አደራ ነው ያሉት አራቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺሕ 900 የአሜሪካ ዶላር ማስረከባቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ምክትል ኢንስፔክተር ዘነበ እሸቱ፣ ምክትል ኢንስፔክተር ዳግም ግርማ እና ዋና ሳጅን ዓለምነሽ ግርማ የተባሉ የአቃቂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት በጥበቃ ሥራ ላይ እያሉ ቆሻሻ ፌስታል ውስጥ የተጠቀለለ 1 ሺሕ 900 የአሜሪካ ዶላር አግኝተው ለጣቢያው አስረክበዋል።


በተመሳሳይም ምክትል ሳጅን ብርቱ ሙዳ በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ ስትንቀሳቀስ በማስክ የተጠቀለለ 2 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር በማግኘቷ ወዲያውኑ ለፖሊስ ጣቢያው ማስረከቧ ተገልጿል።የፖሊስ አባላቱ በሠሩት አርዓያነት ያለው ተግባር ታላቅ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይም ተግባራቸውን አጠናክረው ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።


የአዲስ አበባ ፖሊስ የቆሙለት ዓላማ የገባቸው እና የመለዮን ክብር የተረዱ አባላት በሚሠሩት መልካም ተግባር ኅብረተሰቡ ከሚሰጣቸው ክብር ባሻገር የተቋሙ ግርማ ሞገሶች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ በመልካም ሥነ ምግባር እና አገልግሎት ዕውቅና ሊሰጣቸው የሚገባቸውን አመራር እና አባላትን ማበረታታት ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *