loading
አስመጪና ላኪ ድርጅቶች አጠቃላይ ኦዲት ሊደረጉ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

አርትስ 07/03/2011
አስመጪና ላኪ ድርጅቶች ኦዲት እንዲደረጉ የተመረጡት የስጋት ደረጃቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው ሲልም
ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ከሆኑት በአስመጪ እና ላኪነት ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች
ጋር በህግ ተገዥነት ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት አካሂዷል።
የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሂሩት መብራቴ በውይይቱ ላይ
እንደገለጹት፥ ከ770 የከፍተኛ ግብር ከፋዮች መካካል 272 የሚሆኑት ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ ናቸው።
የህግ ተገዥነት የስጋት ደረጃቸው ከፍተኛ በመሆኑ ኦዲት እንዲደረጉ ከተመረጡት ግብር ከፋዮች መካል
46 የሚሆኑት በአስመጪ እና ላኪነት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች መሆናቸውን ወይዘሮ ሂሩት መብራቴ
ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *