loading
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መብረዱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መብረዱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ

አርትስ 12/03/2011

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት ዲሳሳ እንደተናገሩት ተፈጥሮ የነበረው ሁከት በመብረዱ ተማሪዎችን ጭምር በማወያየት ችግር ፈጣሪዎቹን ለመለየት እየተሰራነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት   እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት በሁለት ተማሪዎች መካከል የተከሰተ ግጭት ሰፍቶ  በአጠቃላይ 34 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ከተጎጂዎቹ ውስጥ የ 29ኙ ቀላል ጉዳት በመሆኑ ወዲያው ህክምና ተደርጎላቸው ተመልሰዋል፡፡5 ያህሉ ደግሞ በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስም በስፍራው ተገኝተው ግጭቱን እንዳረጋጉት ተሰምቷል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *