አቤ ጃፓንን ለረጂም ጊዜ የመምራት ክብረ ወሰን ለመያዝ ተቃርበዋል
አርትስ 10/1/2011
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ የፓርቲያቸው ፕሬዝዳንት ሆነው ዳግም ተመርጠዋል፡
ጠቅላይ ሞኒስትሩ ከ 807 የፓርቲያቸው አባላት ውስጥ የ553ቱን ድምጽ በማግኘት የሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲን ዳግም ለመምራት የሚያስችላቸውን መተማመኛ አግኝተዋል፡፡
ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው አቤ የፓርቲያቸው ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸው መቀጠል ያስችላቸዋል፡፡
ሽንዞ አቤ ለፓርቲ አባሎቻቸው በቀጣዩ የስራ ዘመናቸው ዜጎቿ የሚኮሩባትና ጠንካራ የሆነች ጃፓንን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ ከናንተ ጋር ጠንክሬ እሰራለሁ ብለዋቸዋል፡፡