loading
አብን የአማራ ህዝብ ጨቋኞችን በካርድ ሊቀጣ ይገባል አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 ሕዝባችን ሰላማዊ እምቢተኝነቱን የቀጠለ ሲሆን የምርጫ ካርድ በማውጣትና ለአብን ድምጹን በመስጠት ጨቋኞቹን ሊቀጣ ይገባል ሲል ፓርቲዉ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል፡፡ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የተደራጀና የተቀናጀ የዘር ፍጅት በማውገዝ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ታላቅ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ያለዉ ፓርቲዉ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ሲያደርግ የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ለተወሰነ ጊዜ ገትቶ መቆየቱንም አስታዉሷል፡፡

«የምርጫ ካርዳችንን በማውጣት ጨቋኞችን በድምጻችን በመቅጣት ሕዝባችን ለፍትኅና ኹለንተናዊ እኩልነት መረጋገጥ የጀመረውን ትግል ዳር እናደርሳለን!» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ አካባቢዎች ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ መጀመሩንም ፓርቲዉ አስታዉቋል፡፡ በዚህም መሰረት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ጎባጣ አቅና ቀበሌ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ዞብል፣ ቃሊም እና
ሚጦ ቀበሌወች፣ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከአዘዞ፣ ጠዳ ማክሰኝት፣ እፍራዝ፣ ሰበሃና አርኖ ጋርኖ፣ በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ፣ በአዊ ዞን ጃዊ ወረዳ እና ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ ቦታ ቀጠና የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡

መላው የአማራ ሕዝብም ዛሬ ላይ እየደረሰበት ያለው መዋቅራዊና ሥርዓታዊ በደል ምንጩ ተገቢ ፖለቲካዊ ውክልና ባለማግኜቱና በኃቀኛ ልጆቹ ባለመወከሉ በመሆኑ የሕዝባችንን ነገ በሚወስነው ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ የምርጫ ካርዱን በማውጣት ገዳዮቹን በድምጹ እንዲቀጣና አብንን በመምረጥ የጀመረውን ሰላማዊ እምቢተኝነት ከዳር ሊያደርስ እንደሚገባ ፓርቲዉ አሳስቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *