loading
አትሌት ሰለሞን ባርጋ የ2018 የዓመቱ ምርጥ ወጣት አትሌት ዕጩዎች ውስጥ ተካተተ

አርትስ ስፖርት 04/03/2011

የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የ2018 ምርጥ ወጣት አትሌቶችን ለመሸለም የመጨረሻዎቹን 5 እጩዎች ይፋአድርጓል፡፡ IAAF በየአመቱ ምርጥ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ለነበሩ አትሌቶች ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ከዚህ በፊት የ2018 የዓመቱ ምርጥ አትሌት እጩዎች ይፋ ሲያደርግ በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውን አትሌቶች አለመካተታቸው ይታወሳል፡፡ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከ20 ዓመት በታች ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል፤ ተስፋ ከተጣለባቸው እጩዎች ውስጥ ሲካተትበ2018 የዳይመንድ ሊግ በ5000 ሜትር 12፡43.02 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ ከ20 ዓመት በታች ክብረ ወሰን በመስበር፤ከ2005 ወዲህ ፈጣኑን ሰዓት አስመዝገቧል፡፡ በዓለም የቤት ውስጥ ሩጫ በ3000 ሜትር ብር፤ የዓለም ከ20 ዓመት በታችውድድር አራተኛና በአፍሪካ ሻምፒዮና ደግሞ የ5000 ሜትር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡ በዕጩነት ከሰለሞን ጋር የሚፎካከሩትኮባዊው የስሉስ ዝላይ ተወዳዳሪ ጆርዳን ዲያዝ፣ ስዊድናዊው የምርኩዝ ዘላይ አርማንድ ዱፕላንቲስ፣ ኖርዌያዊው የመካከለኛናረዥም ርቀት ሯጭ ጃኮብ ኢንገብሪትሰን እና ኬንያዊው አትሌት ሮኔክስ ኪፕሩቶ ናቸው፡፡ የ IAAF የአትሌቲክስ ሽልማት ስነስርዓት እ.አ.አ ታህሳስ 04/2018 በሞናኮ ይደረጋል፡፡ IAAF

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *