loading
አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በደገሀቡር ከተማ 04 ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በትውልድ ከተማቸው ደገሀቡር ምርጫ ጣቢያ 04 ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በደገሃቡር ከተማ የምርጫ ክልል 51ሺህ 292 ህዝብ በመራጭነት ተመዝግበዋል። መራጮች ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እየሰጠ ነው። በተመሳሳይ በጌዴኦ ዞን በቡሌ ምርጫ ክልል ድምፅ የመስጠት ሰራው እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ከ58 ሺህ በላይ መራጮች ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ መራጮችም ሁሉም የተፎካካሪ ፖርቲዎች የኛን ድምፅ ማክበር አለባቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *