አቶ ፍፁም አረጋ ወደ ቀድሞ የስራ ሃላፊነታቸው ተመለሱ
አቶ ፍፁም አረጋ ወደ ቀድሞ የስራ ሃላፊነታቸው ተመለሱ
አርትስ 26/02/2011
የጠቅላይ ሚንስትሩ የፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ፍፁም አረጋ ከጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኃላፊነት ተመልሰዋል፡፡
አቶ ፍፁም ከዚህ በፊት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ለአዲሱ ኃላፊነት እንግዳ አይሆኑም።
የጠቅላይ ሚንስት አብይ አህመድን ፅህፈት ቤት በሃላፊነት ከተረከቡበት ከሚያዚያ ወር ወዲህ በቆዩባቸው ሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ አጫጭር መረጃዎችን በማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን በተለይ በቲዩተር እና ፌስቡክ ገጻቸው በፍጥነት ለማህበረሰቡ በማሰራጨት የሚታወቁ ከመሆኑም በላይ ለተለያዩ ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሃንበሚሰጧቸው ወቅታዊ ምላሽ የተሰጡትን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈትቤት በከፍተኛ ብቃት ሲመሩ እንዲቆዩ ተገልጿል።
በእንግሊዝ ሀገር በማንቼስተር ዩኒቨርሲቲ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ድግሪ ምሩቅ የሆኑት አቶ ፍፁም ቀደም ብለውም የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኤጄንሲና የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ በሮ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆንም አገልግለዉ እንደነበር ይታወቃል።
በምትካቸውም አቶ ሽመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፅህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው እንደሚሰሩ አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡