loading
አንጎላ በአንድ ሳምንት ውስጥ 380 ሺ ህገ-ወጥ ስደተኞች ከሃገሯ መውጣታቸውን አስታወቀች

አርትስ 12/02/2011

የአንጎላ  መንግስት በህገወጥ የአልማዝ ነጋዴዎች ላይ ባደረገው ዘመቻ 380 ሺ ህገ-ወጥ ስደተኞች ሀገሪቷን ለቀው መውጣታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

ከነዚህ ስደተኞች ውስጥም አብዛኞቹ የጎረቤት ሀገር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎች ሲሆኑ ስደተኞቹ ሀገሪቷን ለቀው የወጡት በፍላጎታቸው ሳይሆን በሀገሪቱ ፖሊሶች ተገደውና ጥቃት ተደርጎባቸዉ ነው ሲሉ እማኞች ለሲጂቲኤን አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት  ደህንነት ሃላፊ እንደተናገሩት  በአካባቢው 231 የሚሆኑት ህገ-ወጥ የአልማዝ ንግድ መደብሮችን በመዝጋት 59 ህገ- ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እና  ዘመቻው በሀገሪቱሰሜንና ምዕራባዊ ግዛቶች ላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ገልፀው የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀምም አስፈላጊው ጥንቃቄ እንደሚደርግ ገልጸዋል፡፡

ስደተኞች በበኩላቸዉ፥ በአንጎላ መንግስት ግፊት ሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ እና  የሃገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች ለ10 ዓመታት  ያፈሩትን ሃብትና ንብረት ቀምው እንዳባረሯቸው በተጨማሪም በሀገሪቱ ፖሊሶችና ወጣቶች በተደረገዘመቻ የስደተኞች ቤት መቃጠሉንና በበርካታ ሰዎች ላይም ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡

የስደተኞቹን አቤቱታ ተከትሎ በሁለቱ ጎረቤት ሀገሮች ድንበር አካባቢ በድሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎችና በአንጎላ የፀጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *