loading
አውሮፓ ህብረት ከቻይና እና አሜሪካ ጋር በአፍሪካ የሚያፎካከረውን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ::

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ያለውን ግንኙነት በእጥፍ እንደሚጨምር የተነገረለትን አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ህብረቱ ይፋ ያደረገው አዲስ ስትራቴጂ በአፍሪካ ንግድ እና ኢንቨስትመንት የቻይና ፣የአሜሪካንና የሩሲያን ድርሻ ለመጋራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አውሮፓ ከአፍሪካ ጋር ያለው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 235 ቢሊየን ዩሮ ቢደርስም በቻይናና በአሜሪካ በአምስት እጥፍ ይበለጣል፡፡

በህብረቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚሽን እና በአፍሪካ አገራት መካከል ምክክር የተጀመረ ሲሆን ውይይቱ በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ ፣ በኢኮኖሚ እድገት እና በስራ ፈጠራ፣ በደህንነት እና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በስደት ቅነሳ ላይ እንደሚያተኩር ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በሚቀጥለው ጥቅምት ወር በብራሰልስ በሚደረገው ስብሰባ ላይ የአፍሪካ መሪዎች እስትራቴጂውን እንደሚደግፉት ተስፋን ሰንቋል፡፡

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ቦሬል ግንኙነታችንን ማጠናከር እንፈልጋለን የእኛ በአፍሪካ አህጉር መገኘት ኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል ልማት አጋር የመሆን ፍላጎታችንን ያሳካል ብለዋል፡፡

ስትራቴጂው የፀጥታ ትብብርን ለማጠናከር እንደ ሊቢያ ፣ ማሊ እና ሶማሊያ ባሉ ሀገራት ውስጥ የረጅም ጊዜ ቀውሶችን ለማስወገድ ይረዳል ነው የተባለው፡፡

ስትራቴጂው አፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚገቡ ያልተፈቀደላቸው ስደተኞች ዋነኛው ምንጭ በመሆኑ በጋራ የሚደረገውን ድንበር ተሸጋሪ ቁጥጥር ያቀለዋልም ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *