loading
አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ሊቨርፑል ከባየር ሙኒክ ሲገናኝ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ከፒ.ኤስ.ጂ ይፋለማል

አርትስ ስፖርት 08/04/2011

የ2018/19 አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ዕጣ ድልድል ዛሬ ከሰዓት በኋላ በኒዮን ይፋ ሁኗል፡፡

በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ የእንግሊዙ ሊቨርፑል ከ ጀርመኑ ባየርን ሙኒክ የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ያደርጋል፤ ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ከ ፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ይፋለማል ተብሏል፤ ባርሴሎና ከ ሊዮን ጋር ይገናኛል፤ ማንችስተርሲቲ ከ ጀርመኑ ሻልከ 04 ሲገናኝ፣ ቶተንሃም ሆተስፐር ከ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ይጫወታሉ፤ ሪያል ማድሪድ ከ አያክስ፣ ሮማ ከ ፖርቶ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

የጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ጨዋታዎች የካቲት 5 እና 6/2011 ሲደረጉ፤ የመልስ ግጥሚያዎች ደግሞ መጋቢት 10 እና 11/2011 ይከናወናሉ፡፡

በምድብ ቀዳሚ ሁነው ያጠናቀቁት አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ባርሴሎና፣ ፒ.ኤስ.ጂ፣ ፖርቶ፣ ባየርን ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ዩቬንቱስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጭ ያደርጋሉ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *