loading
አይቮሪኮስታዊያን ፍትህ ከወዴት አለሽ እያሉ ነው

አርትስ 03/ 03/2011

 

የዘገየ ፍትህ እንደቀረ ይቆጠራል ቢባልም ኮትዲቯራዊያን ግን ፍትህን እንደናፈቁ አመታት ተጥቆረዋል፡

በአይቮሪኮስት ሁለተኛው የርስርበርስ ጦርነት በፈረንጆቹ 2011 ነበር የተካሄደው፡፡

በወቅቱ ሀገሪቱን ይመሩ በነበሩት ፕሬዝዳንት ላረውነን ባግቦ እና በተቃዋሚው አላሳኒ ኦታራ መካከል በተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት በትንሹ 3 ሺህ ሰዎች መስዋእት ሆነዋል፡፡

አልጀዚራ እነደዘገበው ያኔ ከሞት የተረፉት እና የስቃይ ሰለባ የነበሩ ሰዎች አሁንም ድረስ ከስነ ልበናዊ ጉዳታቸው ማገገም ተስኗቸዋል፡፡

በዚህ የእርስበርስ ጦርነት ወቅት መንግስትን ወይም ተቃዋሚን መደገፍ ሁለቱም ጉዳት ያስከትላል፡፡ ምክንያቱም አንዱ ሌላውን መደገፍ ብቻ ግርፋት፣ ለአስገድዶ መደፈር ከፍ ሲል ደግሞ ለሞት ሰለባነት ይዳግ ስለነበር ነው፡፡

ታዲያ በዚያን ጊዜ ከፍተኛ ስቃይ የደረሰባቸው ቸዎች ተስፋ ሳይቆርጡ ያኔ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ለህግ እነዲቀርቡና እነሱም አንዲካሱ አሁንም የፍትህ እየለህ እያሉ አቤት ማለታቸውን አላቆሙም፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *