loading
አደንዛዥ ዕጽ በሱዳን ድንበር እንዳይገባ እየተቆጣጠርኩ ነዉ-ፌዴደራል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 የአደንዛዥ ዕጽ በሱዳን ድንበር እንዳይገባ እየተቆጣጠረ መሆኑን ፌዴደራል ፖሊስ ገለጸ የፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በሱዳን ድንበር ህብረተሰቡ ጁንታው እንደ ትልቅ መሳሪያ የሚጠቀምበትን የአደዛዥ ዕጽ እንዳይዘዋወር ድንበር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በሱዳን ድንበር ተከዜ ማዶ የመሸገውን አሽባሪ ቡድን እቅስቃሴ በመከታተልና አጸፋዊ ምላሽ በመስጠት ተልዕኮውን እየተወጣ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሮክቶሬት ዲቪዥን 3 ሃላፊ ኮማንደር እንየው አለባቸው ተናግረዋል፡፡

በሁመራ ግንባር የተሰለፈው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የሽብር ቡድኑና ተላላኪዎቹ በሱዳን ድንበር ወደ ሀገራችን እንዳይገቡና ወደ ሱዳንም እንዳይሻገሩ መፈናፈኛ በማሳጣት ተስፋ እያስቆረጣቸው መሆኑን ጨምረው ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
ቡድኑ በማይካድራ፣ሁመራና አካባቢው የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሞ ወደ ሱዳን በመሻገር ሀይሉን ለማጠናከር ቢሞክርም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ልዩ ሀይል ጋር በመሆን የወረራና የተስፋፊነት ህልሙ እንዲጨናገፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ጦርነቱ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ እንደገና ወረራ እየፈፀመ ካለ ሃይል ጋር በመሆኑ ህብረተሰቡ በንቃትና በትጋት ለሰራዊቱ መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ጨምረው አመላክተዋል፡፡ ህብረተሰቡ የሽብር ቡድኑ እንደትልቅ መሳሪያ የሚጠቀምበትን የአደዛዥ ዕጽ እንዳይዘዋወር ድንበር ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል፡፡ለዚህም ለሁመራና አካባቢው ማህበረሰብ ምስጋና ይገባልም
ብለዋል፡፡ ይህንን ቡድን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣትና እስከመጨረሻው ለማጥፋት መስዋትነትም ጭምር ለመክፈል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *