loading
አደጋ በደረሰበት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተገኘ

አደጋ በደረሰበት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተገኘ

አርትስ 19/02/2011

 

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን  በገንዳ ውሀ ከተማ  አደጋ ደርሶበት በተገለበጠ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ በርካታ የጦርመሳሪያ  እና ገንዘብ መገኘቱን የመተማ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል  ።

ተሽከርካሪው ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን፥ በገንዳውሀ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ኢንዱስትሪ መንደር በሚባል አካባቢ በትናትናው ዕለት ፍየል አድናለሁበሚል ምክንያት በመገልበጡ አደጋ ደርሷል ተብሏል።

የከተማ አስተዳደሩና የወረዳው የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ፍተሻ መሰረት 97 ክላሽን ኮፍ፣ 1 ሺህ 291 የቱርክ ሽጉጥ እና 3 ብሬን መገኘቱንም ነው ፅ/ቤቱ ጨምሮ ያስታወቀው ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *