loading
አዲሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆን…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት በሚኒ ባስ እና በሚዲ ባስ ተሸከርካሪዎች ከ50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ50 ሳንቲም ጭማሪ ስለመደረጉ ተነግሯል፡፡ ጭማሪው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አገልገሎት ሰጭዎች ካጋጠሙ ማህበረሰቡ ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ ቢሮው አሳስቧል፡፡


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ይርጋለም ብርሀኔ ሰለ ማሻሻያው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ህግን ተላለፍው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል። በመግለጫቸውም በመዲናዋ የሚኒቀሳቀሱ ማናቸውም የህዝብ መገልገያዎችንና የጭነት ተሸከርካሪዎችን መዝግቦ መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም የሚወጣውን መመሪያ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ነው ያብራሩት፡፡ የትራንስፖርት አገልገሎቱን የተሳለጠ አሰራርና ደንብን የተከተለ ለማድረግ ለሚደረገው ጥረት የማህበረሰቡና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጠናከር ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *