loading
አዲስ አበባ የአድዋ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ወንድሞቻችን ጭምር  መሆኑን  ለዓለም መድረክ በተገኙ አጋጣሚዎች ሁሉ የማስተዋወቅ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ ከንቲባ ታከለ ኡማ ገለጹ

አዲስ አበባ የአድዋ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ወንድሞቻችን ጭምር  መሆኑን  ለዓለም መድረክ በተገኙ አጋጣሚዎች ሁሉ የማስተዋወቅ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ ከንቲባ ታከለ ኡማ ገለጹ

ከንቲባዉ ስለ አድዋ እና የአድዋ ፌስቲቫል  መልእክት አሰተላልፈዋል ሙሉ መልእክቱ እነሆ፤-

በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር አንድላይ ሆነን የምንዘምርበት፣ የምንጫወትበት እና እየተዝናናን ሃሳብ የምንለዋዋጥበት የጋራ መድክ –አዲዋ ፌስቲቫል!

እንዲህ አይነቱ ድግስ (ፌስቲቫል) በሀሳብ የረቀቀ፣ በእውቀት የበሰለ እና በክውን ጥበባት ትውልድን ከትላንት ጋር በማነጋገር የማንነት ሰብዕናውን እንዲፈትሽ፣ለነገ የምትተርፍን ሃገር ለመስራት ከራስ ጋር ለመመካከር እድል ይሰጣል።

ኢትዮጵያውያን በየዘመኑ የገጠሙንን ፈተናዎች በጋራ ትግል በማለፍ እዚህ የደረስን ህዝቦች ነን።ምስክሩም ዓድዋ ነው።
ከወራሪ ቅኝ ገዢዎች ጋር ተፋልመን ደምና አጥንት ገብረን በነፃነቷ የምትኮራ አገር ባለቤት ሆነናል።
አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሲከፋፈሉ ኢትዮጵያ ደግሞ ያንዱ ድርሻ ልትሆን ወራሪ ኃይል ባህር አቋርጦ ቢመጣም በኢትዮጵያውያን ከልዩነት ይልቅ አንድነትን መርጠው በተባበረ ክንድ መክቶ መልሶታል።
ያንን ጦርነት በመሳሪያ ብልጫ ሳይሆን በሞራልና ሃሳብ ልዕልና ነው። ያንን ጦርነት ያሸነፍነው በፍቅርና በህብረት ነው።
ስለዚህ ለሀገራችን የሰላምና የአንድነት ዋጋ ስልሚመሰክርልን፣ ለከተማችን ደግሞ ልዩ ድምቀትን በመፍጠር ከሌሎች ወንድም እህቶቻችን ጋር አብረን የምናከብርበት አውድ ስለሚፈጥርልን በአብሮነት ማክበርን መርጠናል።

የሰው ልጆች ክብር የሚገለጥበት፣ የዓደዋን ቱሩፋቶች የምንቋድስበት፣ተመራጭ ዓለማቀፋዊ መድረክ እንዲሆንም በቀጣይነት ለመስራት መደላድል የሚፈጥርበት ታሪካዊና ልዪ ዕድል ነው።
አዲስ አበባችን የአድዋ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ወንድሞቻችን ጭምር እንደ ሆነ ለዓለም መድረክ በተገኙ አጋጣሚዎች ሁሉ የማስተዋወቅ ኃላፊነቷን እንደምትወጣ አረጋግጥላችኋለሁ።
እግዚአብሔር ሃገራችንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

ምንጭ ከንቲባ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *