አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ13 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆቹ አካዳሚክ ጉባኤዎች ተፈትሾና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን መረጃ ተመልክቶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡
በዚህም መሠረት፡-ፕሮፌሰር ተሾመ ሶሮመሳ፣ፕሮፌሰር አሰፋ ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ወርቅነህ ቀልቤሳ፣ፕሮፌሰር በቀለ አበበ፣ፕሮፌሰር ዳንኤል አሥራት፣ፕሮፌሰር ንጉሴ መገርሳ፣ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ለማ፣ፕሮፌሰር ጥላሁን ተክለኃይማኖት፣ፕሮፌሰር አበበ በቀለ፣ፕሮፌሰር ኃይሉ ወርቁ፣ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሴ፣ፕሮፌሰር ላይከማርያም አስፋውና ፕሮፌሰር አባተ ባኔ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማግኘታቸውን ነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውጭ ግንኙነት፣ ትብብርና ኮሙዩኒኬሽን ፅሕፈት ቤት የገለፀው፡፡