loading
አፈ ጉባዔዋ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አቀራረብ ህገመንግስቱን የተከተለ አይደለም አሉ

አርትስ 15/02/2011

 

የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክርቤት የቀረበው በአማራ ክልላዊ መንግስት መሆኑ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ያልጠበቀ ነው ሲሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ተናገሩ ፡፡

እንደ አፈጉባኤዋ ገለጻ የማንነት ጥያቄዎች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረብ ያለባቸው ጥያቄውን የሚያነሱ ዜጎች በሚኖሩበት ክልል ከታየ በኋላ ቢሆንም ጉዳዩን እያነሳ ያለው የአማራ ክልል መሆኑ ግን ስህተት ነው።

በመሆኑም ዜጎች እተሰቃዩ ያሉት በክልላቸው በትግራይ በመሆኑ ጥያቄው የሚነሳበት የትግራይ  ክልል  ለዜጎች መቆርቆር እና ጉዳዩን መመልከት ይኖርበታል ነው ያሉት፡፡

አፈ ጉባዔዋ አያይዘው እንደተናገሩት የራያ  የማንነት ጥያቄ እስካሁን ለምክር ቤቱ አልቀረበም ። መቅረብ ያለበትም በሚኖሩበት ትግራይ ክልል ነው። ስለሆነም ክልሉ ይህን ማድመጥአለበት ነው ያሉት አፈጉባኤዋ ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *