loading
ኢሚግሬሽን “ለትግራይ ተወላጆች አገልግሎት መስጠት አቁሟል” መባሉን “ውሸት ነው” አለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለትግራይ ተወላጆች የሚሰጠውን አገልግሎት አቁሟል በሚል በማህበራዊ ሚድያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ፍጹም ሀሰት” እንደሆነ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዪኒኬሽን ዳይሬክተር ደሳለኝ ተሬሳ ተናገሩ፡፡
አቶ ደሳለኝ ለአል-ዐይን እንደተናገሩት በክልሉ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት “ትግራይ” የሚለው ስም ከኤጀንሲው የአገልግሎት ማመልከቻ ድረገጽ ወጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ለትግራይ ተወላጆች አገልግሎቱን በቀላሉ በኦንላይን ለመስጠት ሳይቻል ቀርቷል፡፡ “የኦንላይን ሰርቪስ እየሰጠን መሆኑ ይታወቃል” ያሉት ኮሚዪኒኬሽን ዳይሬክተሩ በክልሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ዳግም ሲጀምር ማንኛውም ሰው አግልግሎቱን የሚያገኝ ይሆናል”ም ብለዋል፡፡ አቶ ደሳለኝ “እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ” እንደሆነም ነው ለአል ዐይን አማርኛ የገለጹት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *