loading
ኢትዮጵያና ቻይና የመሬት ምልከታና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና የመሬት ምልከታና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክትር ዶ/ር ሰለሞን በላይ እና የቻይና ሮኬት ካምፓኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ቺንፒንግ ፈርመውታል።

ግንባታው በኢትዮጵያና ቻይና ባለሙያዎች ትብብር የሚከናወን ሲሆን 50 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴት እንዲጠቀም ይደረጋል ነው የተባለው።

በግንባታው የሚሳተፉ ኢትዮጵውያን ከቻይና የቴክኖሎጂ ልምዱን ይወስዳሉ ተብሏል። ተጠቃሚ መለየት፣ ማስተባበር፣ ፍላጎትና ቦታ መረጣ የመሳሰሉት ተግባራት ሰኔ ወር ላይ ይጀመራሉ።

የአሁኑ የሳተላይት ግንባታ ስምምነት ሳተላይትን የስራ እድል መፍጠሪያ እና ሃብት ማመንጫ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።

አንደ ኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ገለፃ  በሁለቱ ሀገራት ትብብር የተሰራችው የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ህዳር 2012 ወደ ህዋ እንደምትልክም ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *