loading
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሁንም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ድል ማድረግን ገፍተውበታል

አርትስ ስፖርት 03/03/2011

በሣምንቱ ማብቂያ ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የውጪ ሃገራት የጎዳናና አገር አቋራጭ ውድድር ተካፍለው ውጤታማ መሆን ችለዋል፡፡

በሊባኖስ – ቤሩት ማራቶን – በሴቶች መድህኔ ደሜ፣ በ2፡29.31 ጊዜ አንደኛ፣ ሰላማዊት ጌትነት፣ 2፡31.42 3ኛ ደረጃ ስትይዝ፤ አለምነሽ ሂርጳ እና ንግስት ሙሉነህ 5ኛና 6ኛ በመሆን ጨርሰዋል፤ ወንዶች ደግሞ ደረሰ ገለታ በ2፡12.33 በሆነ ጊዜ ሶስተኛ ሲወጣ፤ ሂርጶ ሸኖ፣ ይሁንልኝ አዳነ አራተኛና አምስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

ቻይና ውስጥ በቻንግዴ ማራቶን -በወንድ፣ 1ኛ፡ አሰፋ ከበደ፣ 2፡14.00 እንዲሁም በሴት፡ 1ኛ ቤቴልሄም ሃጂ፣ 2፡38.00 በመውጣት አሸናፊ ሁነዋል፡፡

በሜክሲኮ ጉዋዳላጃራ ማራቶን – በሴት ዘውድነሽ አየለ፣ 2፡41.48 1ኛ፤ በወንድ፡ ሙላቸው አለማየሁ 2ኛ፤

በቱርክ ኢስታንቡል ማራቶን፣ በቻይና -ሄፊ ማራቶን፣ ግሪክ ላይ የአቴንስ ማራቶን እና በጣሊያን ላይ ደግሞ በራቭና ማራቶን አትዮጵያውያኑ መልካም ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ሞሮኮ – ታሜስና ግማሽ ማራቶን – በሴቶች፡ 1ኛ፡ ጽጌ ኃይሌ፣ በ1፡10.40 ጊዜ፣ 2ኛ፡ መሰረት ድንቄ፣ 1፡11.38 በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ ታንገር ግማሽ ማራቶን – ሞሮኮ ላይ ሲካሄድ በሴት፡ ጠጂነሽ ቱሉ፣ 1፡14.37 አንደኛ ወጥታለች፡፡

በቻይና ሌሻን ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን – በወንድ፡ 1ኛ አደላድለው ማሞ፣ 1፡07.45፤ በሴት፡ 1ኛ መልካም ዋለ፣ በ1፡17.26፣ 2ኛ ቃልኪዳን አዲስ፣ በ1፡18.24፣ 3ኛ የኔወርቅ ሁሴን፣ በ1፡20.46 ሰዓት ተከታትለው ገብተዋል፡፡

በሰፔን አገር አቋራጭ ዲ አታፑርካ – በሴት፡ 1ኛ ሰንበሬ ተፈሪ፣ 25፡51፤ 6ኛ በላይነሽ ኦልጂራ፤ በወንድ፣ አባዲ ሃዲስ፡ 4ኛ ሙክታር ኢድሪስ፡ 7ኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ መረጃውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ African Athletics United Page ጠቅሶ አድርሶናል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *