ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በሙሉ የመዳረሻ ቪዛ መሥጠት ጀመረች
አርትስ 23/02/2011
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት አገልግሎቱ መጀመሩን ባበሰሩበት ወቅትእነዳሉት፤ ኢትዮዽያ ለአፍሪካ ሀገራት ዜጎች የመዳረሻቪዛ መስጠት መጀመሯ ፓን አፍሪካኒስትነቷን ዳግም እያጠናከረች ለመሆኑ ማሳያ ነው ።
ሊቀመንበሩ ኢትዮዽያ የፓን አፍሪካኒስት እንቀስቃሴ ባለውለታ መሆኗን አስታውሰው፤አሁንም የህብረቱ መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን ባለውለታም ጭምር ያደርጋታል ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል አገልግሎቱን የጀመሩ እንደነ ሩዋንዳና ጋና እንዲሁም ሞሪሽየስ ቢኖሩም፤የኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ወሳኝንት አለው ብለዋል፡፡ ይህ ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በአጭር ጊዜ ውስተጥ ወደ ስራ መግባቱ ደግሞ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲደነቁ ያደርጋቸዋል፤ አርዓያነታቸውም ለኛም ጭምር ነው ብለዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በበኩላቸው፥ ኢትዮዽያ በአፍሪካ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር እየሰራች ካለችውና ለመስራት ለምታቅዳቸው ስራዎች ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በተቻላት ሁሉ ለማጠናከር ወደ ኋላ እንደማትል አንዱ መሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የመዳረሻ ቪዛው በዋናነት ወጣቶችና ሴቶች በአህጉራቸው የራሳቸዉን የስራ እድል እና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲፈልጉና እንዲፈጥሩ የሚያስችልነውም ብለዋል።
ህገወጥነት እንዳይሰፋፋና ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችንም ቀድሞ ለመከላከል ሃሪቱ ባለችበት አቋም ሙሉ ዝግጅት መደረጉንና ቀድመው አገልግሎቱን ከጀመሩ ሃገራት ልምድ መወሰዱን አሳውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ሌሎች ሃገር ውስጥ ያሉ መንግስታዊ ተቋማት ለስራው ስኬት ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውንና አብሮ የመስራት ሂደቱ መቀጠል እነዳለበት ወይዘሮ ሂሩት ለአርትስ ተናግረዋል፡፡