loading
ኢትዮጵያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት የመጀመሪያዋን ሳተላይት ወደ ህዋ እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ
ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
ኢንስቲትዩቱ ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ የሚያስችለውን ዓለም አቀፋዊ ፈቃድ ማግኘቱን
አስታውቋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮጵያ እና ቻይና መሀንዲሶች
በጋራ በመሆን ወደ ህዋ የምትመጥቀውን ሳተላይት የመገንባት ተግባርን እያገባደዱ ነው፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥቅምት 15 ቀን 2019 ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሳተላይት ወደ ህዋ
ታመጥቃለች ፡፡
70 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሳተላይቷ፤ለግብርና ፣ለውሃ፣ለማዕድን፣ለከተማ ልማት እና ለአየር
ንብረት ቁጥጥርና ክትትል መረጃዎችን የማቀበል ስራ ታከናውናለች፡፡
ሳተላይቷ ኢትዮጵያን በአራት ቀናት፤ዓለምን ደግሞ በ54 ቀናት በመዞር ስራዋን ታከናውናለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *