loading
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቁም እንስሳት ሃብት ብዛት ቁጥር አንድ ብትሆንም የዜጎቿ የነፍስ ወከፍ የስጋ ተጠቃሚነት እጅግ ዝቅተኛ ነው ተባለ

ይህ የተባለው የእርሻና የቁም ከብት ሃብት ሚንስትሩ አቶ ሰይፉ አሰፋ አራተኛው የአፍሪካ የቁም እንስሳት  አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በኢትዮጵያ  የእንስሳት ውጤቶች ፍላጎት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቷል፤ በአንፃሩ የሀገር ውስጥ ምርት  የህንን ፍላጎት  ማሟላት  የሚያስችል ዕድገት አልታየበትም ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ከጥቅምት 8  እስከ 10 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው አራተኛው የአፍሪካ የቁም እንስሳት  አውደ ርዕይ በዘርፉ በርካታ ልምድ  ያለቸው ከ 13 የአለም ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች  ተሳትፈውበታል፡፡

በአውደ ርዕዩ የሶስት ቀናት  ቆይታ ከውጭ ሀገራት የመጡ ግዙፍ  ኩባንያዎች  ከሀገር ውስጥ የስጋና የከብት ውጤቶች አቅራቢዎች ጋር  ችግር ፈቺ የሆኑ ውይይቶችና የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሏል ። አውደርዕዩን 5 ሺ ሰው ይጎበኘዋል ተብሎም  ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *