loading
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአውሮፓ ህብረት የጋራ አለም አቀፍ የቢዝነስ ት/ቤት ለመክፈት ተስማሙ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአውሮፓ ህብረት የጋራ አለም አቀፍ የቢዝነስ ት/ቤት ለመክፈት ተስማሙ

አርትስ 27/03/2011

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን የኢትዮ-አውሮፓዊያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤትን ለመመስርት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/መድህን እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን መሪ ጆን ቦርግስታም ናቸው የተፈራረሙት፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ድህረ -ገፅ ዘገባ፤ በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያዊያንን በማስተርስ ደረጃ ከኢትዮጵያ አቬሽን አካዳሚ የቢዝነስ አስተዳደር መከታተል ያስችላል፡፡

አቶ ተወልደ ለኢትዮጵያ አቬሺን አካዳሚ ማጠናከሪያነት በአውሮፓ ህብረት የተገኘው ድጋፍ አለም አቀፍ ደረጃ ያለው የMBA መርሃ ግብር መስጠት ያስችለናል ብለዋል፡፡

በዚህም አቬሺን አካዳሚው የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማገልገል እንደሚያስችለው አስረድተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ቡድን መሪ ጆን ቦርግስታም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቬሺን አካዳሚ አጋር በመሆናችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡ይህም የአገሪቱን የስራ እድል ፈጠራ ለማገዝ የሚደረገውን ጥረትና ስራ ፈጣሪ ትውልድ ለማፍራት በር የሚከፍት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አቬሺን አካዳሚ አሁን ከሚጀምረው የአዲስ የቢዝነስ አስተዳደር የሁለተኛ ድግሪ መርሃ ግብር ባሻገር፣ በአውሮፕላን አብራሪነት፣በአስተናጋጅነት፣በንግድ እና በበረራ ጥገና በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *