loading
ኢትዮጵያ ዉስጥ ሁሉንም ክልሎች ያሳተፈ የፖለቲካ መዋቅርያ ያስፈልጋል አለ፡፡

ይህንን ያለዉ የጋምቤላ ክልል ንቅናቄ ዛሬ በሰጠው መግለጫላይ ነው
አርትስ 03/01/2011
የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ ድርጅት በውጪሃገራት ያሉ እና በየደረጃው የሚታገሉ አካላት ወደ የሃገራቹ ግቡ የሚለዉ ጥሪ ከተደረገ በኋላ ነው ወደ ሃገር ውስጥ የገባው፡፡
የድርጅቱ ቃል አቀባይ አቶ ኡቤንግ አኩሙ እንደተናገሩት በሃገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ተግባራዊ እንዲሆን እና ሁሉንም ብሄር ያሳተፈ የፖለቲካ መዋቅር እንዲዘረጋ በጋራ ለመስራት ነው ወደሃገር ውስጥ የገባነው ብለዋል፡፡
ድርጅቱ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ታጣቂዎች እንዳሉት የገለፀ ሲሆን ከመንግስት ጋር ያለው ሂደት እስከሚያልቅ በውጭ ያሉ ታጣቂ ሃይሎቼ ወደሃገር ውስጥ አልገቡም ብሏል፡፡
የጋምቤላ ማህበረሰብ ማእከላዊ መንግስት እና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆን መደረግ አለበትም ብለዋል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በቅንጅት የመስራት እና ወደ ጋምቤላ በመሄድ ወጣቱን የማወያየት ስራ እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *