ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝደንት ሾመች
አርትስ 15/02/2011
አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ 4 ኛዋ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ዛሬ ተመርጠዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፈረንሳይ ሀገር ባገኙት ነጻ የትምህርት ዕድል ተከታትለዋል፡፡ ስራቸውን የጀመሩት ደግሞ በትመህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ በመሆን ነው፡፡
በመቀጠልም በውጭ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ሴት አምባሳደር በመሆን ጀቡቲ ፤ሴኔጋል ፤ሞሮኮ እና ቱኒዚያ አግልገለዋል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ውስጥም የኢትዮጵያ ተጠሪ በመሆን ሰርተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህል እና የትምህርት ድርጅት(ዩኔስኮ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ በመሆን ሰርተዋል በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ በርካታ ልምድ ያለቸው ሴት እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል፡፡
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ከአፍሪካ የመጀመሪያ ሴት ተወካይ ናቸው።
ለብዙ ዘመናትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የሁለት ልጆች እናት የሆኑት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለረጅም ጊዜ በተለያዮ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪየአፍሪካ ሃገራት የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።እ .ኤ .አ በ2011 ደግሞ በወቅቱ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ የነበሩት ባን ኪሙን በናይሮቢየተባበሩት መንግስታት ጽ /ቤት ዋና ኃላፊ የስራ መደብ ሾመዋቸው ለዓመታት አገልግለዋል።
በቅርቡ ደግሞ በአፍሪካ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይነት እያገለገሉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል ፤ ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውምተሰምቷል።
ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡