ኢትዮጵያ የተመድ ሰላማዊ የህዋ አጠቃቀም ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች
አርትስ 06/03/2011
ኢትየጵያ ህዋን ለሰላማዊ ጥቅም ብቻ በተለይም ለልማት እንዲውል በሚከታተለው የተባበሩት መንግስታትድርጅት ኮሚቴ አባል ሆና መመረጧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ የኮሚቴው አባል ሆና መመረጧም በህዋ አጠቃቀም ረገድ እያከናወነች ላለው እንቅስቃሴዎች ዓለምአቀፍ ድጋፍና ዕውቅና የሚያስገኝላት ይሆናል ተብሏል።
ሳተላይት ለኢንዱስትሪዎች የሚመቹ ቦታዎችን፣ የግብርና ምርትን እና የውሃ ሃብትን የመሳሰሉ ዝርዝርመረጃዎችን ያቀብላል። የተለያዩ መረጃዎችን በፍጥነት ከማስገኘቱም በላይ ድካምን ይቀንሳል ወጭንምይቆጥባል፡፡