loading
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት – የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት ሲሉ የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። በወቅቱም የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት መሆኗን አንስተው፥በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ጉዳዮች ሁሉም አፍሪካውያን በትኩረት የሚመለከቱት ጉዳይ ነው ብለዋል።

አምባሳደሯ ህወሓት በሃገርና በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የሽብር ተግባር በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለሚታይ ወገንተኝነትና ያልተገባ ጫናን በተመለከተ ለሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም መንግስት ለትግራይ ህዝብ ደህንነት በማሰብ የወሰነውን የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት በመናቅ የሽብር ቡድኑ ህጻናት ልጆችን በጦርነት እየማገደ፣ አጎራባች ክልሎችን በማጥቃት ንፁኃን ዜጎችን በመግደልና በመዝረፍ የሽብር ድርጊቱን እንደቀጠለበት ጠቅሰዋል።
ከዚህም አልፎ ኢትየጵያን ለማፍረስ ከውጭና ከውስጥ ተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ህብረት በመፍጠር አካባቢውን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየሞከረ እንደሆነ ይህም ለአካባቢው ሀገራትም ስጋትና አደገኛ ስለሆነ በጋራ ሊወገዝ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እኔ ብቻ ልጠቀም በሚል ስለ ህዳሴ ግድቡ ትክክል ያልሆነ መረጃዎችን በማሰራጨትና በኢትዮጵያ ላይ ግፊት በማድረግ የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅ ለማስተጓጎል እየሰሩ ነው ብለዋል። የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ሉአላዊት ሃገር መሆኗን በመጥቀስ፥ የትግራይ ጉዳይ የውስጥ
ጉዳይ መሆኑንና የሚደረጉ አላስፈላጊ ጫናዎችና ጣልቃ ገብነቶች ተቀባይነት እንደሌላቸውም አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በአፍሪካዊ ወንድማማችነት መደጋገፍ እንጂ ከመርህ ውጪ የሆነ ጣልቃ-ገብነት ተገቢ አለመሆኑን አስምረውበታል። በተጨማሪም ሚኒስትሩ የአባይን ውሃ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በብቸኝነት ለመጠቀም የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት ኡጋንዳ በፍፁም እንደማትቀበል መግለፃቸውን። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *