loading
ኢትዮ-ቴሌኮም ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

አርትስ 29/12/2010
ኢትዮ-ቴሌኮም ሀገር ቤት ለገቡና በመግባት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ኢትዮ-ቴሌኮም በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡
ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎቱ የድምጽ፣ የዳታና የአጭር መልዕክት ያጣመረ ፓኬጅ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ 
ኢትዮ-ቴሌኮም ያቀረበው ልዩ የዲያስፖራ አገልግሎት ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጨምሮ ዝግጅቱ ባጠናቀቀባቸው የተለያዩ ሆቴሎች በቅርቡ ለአዲስ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ለገቡና በመግባት ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ በሌሎች ሆቴሎች በተመሳሳይ ሁኔታ አገልግሎቱን እንደሚጀምር ገልጿል፡፡
በቀጣይ ለጎብኚዎች በቋሚነት የሚቀርብ ልዩ አግልገሎት ከጥቅምት 1ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተቋሙ አመልክቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *