loading
ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በአልጋርቭ ዋንጫ ውድድር ላይ ትዳኛለች ተባለ

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በአልጋርቭ ዋንጫ ውድድር ላይ ትዳኛለች ተባለ

አትዮጵያዊቷ ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በ2019ኙ የአልጋርቭ ዋንጫ ካፍን ከሚወክሉ ዳኞች መካከል ተካትታለች ተብሏል፡፡

የአልጋርቭ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 27 እሰከ መጋቢት 06/2019 በፖርቱጋል አስተናጋጅነት በሚካሄደው ውድድር በዋና ዳኝነት ዘጠኝ ዋና ዳኞች ከዘጠኝ የተለያዩ ሀገራት እንዲሁም 18 ረዳት ዳኞች ከአስራ አራት ሀገራት ተመራጭ ሆነዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ አባል ሀገራት ውስጥ ለውድድሩ ከተመደቡት ዋና ዳኞች መካከል የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን /ካፍ/ን ከሚወክሉት መካከል አንዷ ሊዲያ ታፈሰ መሆኗን ማህበሩ በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በተለያዩ የዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ  እግር ኳስ ውድድሮች ላይ  ጨዋታዎችን በመምራት መልካም ስም እየገነቡ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የካፍ አርቢትሮች መካከል ትጠቀሳለች፡፡

መረጃውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአርትስ አድርሷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *