loading
ኢከር ካሲያ ከሆስፒታል ወጥቷል

የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ስፔናዊው ኢከር ካሲያ፤ ባለፈው ሳምንት ዕረቡ ከክለቡ ፖርቶ ጋር ልምምድ እየሰራ ድንገተኛ የልብ ድካም ገጥሞት ሆስፒታል መግባቱ ይታወሳል፡፡

የዓለም ዋንጫን ከስፔን ጋር ያሳካው የ37 ዓመቱ አንጋፋ ግብ ጠባቂ፤ ከህክምና ክትትል በኋላ ከሆስፒታል የወጣ ሲሆን በሰጠው መግለጫ ለተወሰኑ ሳምንታት አሊያ ወራት ዕረፍት ማድረግ እንዳለበት ተናግሯል፡፡

ኢከር ካሲያ ያስተናገደው የልብ ድካም ህመም አይነት በህክምና ባለሙያዎች አጠራር Acute myocardial infarction የሚሰኝ ሲሆን ወደ ልብ ጡንቻ የሚፈሰው ደም በድንገት ሲቋረጥ ህብረህዋሳት ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው፤ በመሆኑም ይህ የልብ ድካም ህመም አይነት የሁልጊዜም ክትትል የሚስፈልገው እንደሆነ ይነገራል፡፡   

ካሲያ ከሆስፒታል ውጭ ሆኖ በሰጠው መግለጫ ትልቁ ነገር አሁን ከእናንተ ጋር ነኝ ወደፊት ግን ምን ሊሆን እንደሚችል አላውቅም፤ አሁን ምንም አልል ሲል አክሏል፡፡

‹‹ከቀናት በፊት አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እገኝ ነበር፤ እንዲህ አይት ነገር ደግሞ በህይወት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊፈጠር ይችላል፤

ግብ ጠባቂው ለባሰ ጉዳት ላለመጋለጡ እና ህመሙ ውስብስብ ላለመሆኑ ለፖርቶ እግር ኳስ ክለብ የህክምና ቡድን አባላት ምስጋናውን ችሯል፡፡

ኢከር ካሲያ ከ16 ዓመቱ ጀምሮ በሪያል ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናቤው ቆይታው 725 ያህል ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ እና አምስት የላሊጋ ዋንጫዎችን አሸንፏል፡፡

ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ደግሞ ሁለት ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫን በ2008 እና 2012 እንዲሁም በ2010 የዓለም ዋንጫን አንስቷል፡፡

በ2015 ማድሪድን ለቆ የፖርቱጋሉን ፖርቶ ከተቀላቀለ በኋላ ባለፈው ዓመት የፖርቱጋል ሊግን ዋንጫ አሳክቷል፡፡ በግል ደግሞ 177 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን በማድረግ ባለክብረወሰን ተጫዋች ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *