loading
ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 ኢዜማ መንግስት የፓረቲያቸዉን አባል ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፉት ባስቸኳይ እንዲያቀርብ ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ የፓርቲዉ አባል አቶ ግርማ ግድያን ተከትሎ በሰጠዉ መግለጫ ፤ ከዚህ በፊት በቢሾፍቱ ከተማ የምናደርገዉ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሙ እና አባላቶቻችን ላይ ማዋከብ ሲያገጥመን የቆየ ነዉ ብሏል፡፡

የምርጫ ወረዳ መዋቅራችን የሚጠቀምበት ጽ/ቤት ለመክፍት ብዙ ዉጣ ዉረድ ብናልፍም ከከተማ አስተዳደሩ በሚደርስ ጫና እንዳልተሳካ ገልጿል፡፡
በተደጋጋሚም ለአስተዳደሩ ፓርቲዉ አቤቱታ ማስገባቱንና ሌሎች ተቋማት ላይም አቤቱታ ማቅረቡን በመግለጫዉ ወቅት ተገልጿል፡፡ ቀጣዩ ምርጫ ፍትሃዊ እንዲሆንም መመሟላት ከሚገባቸወዉ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ በሚደረግባቸዉ አካባቢዎች በነጻነት መንቀሳቀስ፤ ለማህበረሰቡ አማራጫቸዉን ማቅርብ መቻል እና ዜጎች ደህንነታቸዉ ተጠብቆ ፤መንቀሳቀስ ሲችሉ መሆኑን የገለጸዉ ፓርቲዉ ፤ የአባላችን መገደል አሁን ብዙ የቤት ስራ እንደሚጠበቀን ማሳያ ነዉ ብሏል፡፡

የሕግ የበላይነት እና ዴሞክራሲ ስርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን የሚደረግ ትግል ብዙዎችን መስዕዋትንት የጠቀ በመሆኑ ፤ በትግስት ፓርቲዉ ለዲሞክራሲ መክፍል ያለበትን መስዥዋትነት እንደሚከፍል በመግለጫዉ ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *