loading
ኢጋድ በሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 ኢጋድ በሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳ:: የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በተቀናቃኝ መሪው ሬይክ ማቻር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እገዳ ሙሉ በሙሉ አነሳ፡፡ እገዳው የተነሳው ጦርነቱ ቆሞ ተቀናቃኝ አካላቱ ከስምምነት ላይ ደርሰው በጋራ መስራት በመጀመራቸው ነው፡፡

በዚህም ማቻር የቀጣናዊው ተቋም  አባል ወደሆኑ ወደ የትኞቹም ሃገራት ለመጓዝ ይችላሉ የቁም እስረኝነቱም ተነስቶላቸዋል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ሲያደርጉት በነበረው ድርድር ከስምምነት ላይ የደረሱት ተቀናቃኞቹ ኃይሎች ባሳለፍነው ዓመት የካቲት ላይ የአንድነት መንግስትን መመስረታቸው የሚታወስ ነው፡፡ በስምምነቱ መሰረት ማቻር የሃገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡ ይህም በኢጋድ ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል፡፡ ኢጋድ ከሰሞኑ በጅቡቲ 38ኛ ልዩ የመሪዎች ጉባዔውን ሲያካሂድ እንደነበር ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *