ኤርዶሀን በኢምፔሪያሊስት ዓለም መኖር አንፈልግም አሉ
ኤርዶሀን በኢምፔሪያሊስት ዓለም መኖር አንፈልግም አሉ
አርትስ 28/02/2011
ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን ይህን ያሉት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቸውን ከምንጊዜውም የከፋ የተባለውን አዲሱን ማእቀብ በመቃወም ነው፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው በአሜሪካ ህግ እንደማትገዛና በኢራን ላይ የጣለቸውን ማእቀብ አጥብቃ እንደምትቃወም ተናግረዋል፡፡
ዋሽንግተን በቴህራን ላይ የጣለቸው ማእቀብ ዓለም አቀፉን ህግ የሚፃረር ነው ያሉት ኤርዶሀን አሜሪካኖች ዓለም ሚዛ ኗን ጠብቃ እንዳትቀጥል ተግተው ይሰራሉ በማለት መረር ያለ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡
በአዲሱ ማእቀብ መሰረት ከኢራን ነዳጅ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ስምንት ሀገራት መካከል የቱርክ ስም ቢካተትም ፕሬዝዳንቱ አሜሪካን ከመውቀስ አልተቆጠቡም ይላል ዘገባው፡፡