loading
ኤዜኩሲሊ የናይጀሪያን ፖለቲካ እታደገዋለሁ አሉ

ኤዜኩሲሊ የናይጀሪያን ፖለቲካ እታደገዋለሁ አሉ

አርትስ 14/03/2011

 ኦቤይ ኤዜኩሲሊ በናይጀሪያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን የውድድሩን ሜዳ ተቀላቅለዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ናይጀሪያ በመጭው የፈረንጆቹ 2019 በምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አንዲት ብርቱ ሴት የማማዱ ቡሀሪ ፈተና ሆነው ብቅ ብለዋል፡፡

ኦቤይ ኤዜኩዚሊ ከሲ ኤን ኤኗ ክርቲያን አማምፖር ጋር ባደረጉት  ቃለ መጠይቅ ናይጀሪያ ሁለት መሰረታዊ ችግሮች አሉባት፤  የምወዳደረውም ሀገሬን ከችግሯ ልታደጋት ነው ብለዋል፡፡

እጩ ተወዳዳሪዋ እንደሚሉት እነዚህ ችግሮች የመልካም አስተዳር እጦትና ስር የሰደደ ሙስና ናቸው፡፡

የትራንስፓረነሲ ኢንተርናሽናል ተባባሪ መስራች የነበሩት ኤዜኩሲሊ ሙስና ከድሆች ኪስ መዝረፍ  መሆኑን ጠንቅቄ ስለምረዳ ብመረጥ ቀዳሚው አጀንዳዬ እሱን ማጥፋት ነው ብለዋል፡፡

ኤዜኩዚሊ በቦኩሀራም ታግተው የተወሰዱ የችቦክ ልጃገረዶችን ለማስለቀቅ ልጆቻችንን መልሱ የሚል ዘመቻ ከፍተው በመታገል በመላው ናይጀሪያዊያን አድናቆትን አትርፈዋል፡፡

ባላቸው ዓለም አቀፍ ልምድና በሀገር ቤት ባገኙት ዝና ታግዘው ማማዱ ቡሀሪንና አቲኩ አቡበከርን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ይሆናሉ የሚሉ ሰወች ከወዲሁ ተበራክተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *