እጅን መታጠብ ለብቻው ከጤና መታወክ አይታደግም ተባለ
ምግብ ከመመገብ በፊትና በኋላ እጅን መታጠብ ቢለመድም ሙሉ ለሙሉ በሽታ የሚተላለፍበትን
መንገድ ለመቆጣጠር ግን አያስችልም አለ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
በሚኒስቴሩ የሃይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዳይሬክተር አቶ ዳኘው ታደሰ እንዳሉት እጅን በመታጠብ
ብቻ በሽታን መከላከል ስለማይቻል የግልና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ አማራጭ የለውም ።
ህብረተሰቡ እጅ መታጠብን ልምድ እንዲያደርግ የተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ
ውጤታማ ለውጥ እንዲታይ አድርጓል ያሉት ዳይሬክተሩ 32 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ግንዛቤውን
አዳብሮ ተግባራዊ ማድረግ እንደቻለም ተናግረዋል።
የተገኘው ውጤት ቀጣይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ያሳያል ብለዋል ።
እንደዳይሬክተሩ የመቀንጨር ችግርን በ 2022 ከኢትዮጵያ ለማጠፋት ታልሞ በተጀመረው ተግባር
እጅን መታጠብ በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተደርሶበታል። በተለይ በአማራና
በትግራይ ክልሎች ተጨባጭ ለውጦች መታየታቸውንም ተናግረዋል።
የዘንድሮው የዓለም እጅ መታጠብ ቀን በመላው ኢትዮጵያ ጥቅምት 10 ቀን እንደሚከበር ሚኒስቴሩ
ይፋ አድርጓል።